ብስኩት ልግዛልሽ ብሎ በማታለል የ5 ዓመት ህፃን ልጅን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ። በሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ብስኩት ልግዛልሽ ብሎ በማታለል የ5 ዓመት ህፃን ልጅን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
 
በሀላባ ዞን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ዛላ ፍሬ ቀበሌ ደነቤ ፋማ ቀጠና ልዩ ስፍራ ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው፡፡
ተከሳሽ  በሀሩ ሽርሞሎ የተባለ ሲሆን  የ5 ዓመት ህፃን ልጅ የሆነችውን ግለሰብ በግምት ከቀኑ 11:00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ዛላ ፍሬ ቀበሌ ደነቤ ፋማ ቀጠና ልዩ ስፍራው ደነቤ ተብሎ በሚጠራበት ስፍራ ብስኩት እገዛልሻለሁ ብሎ በማታለል የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀሙን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኑርዬ ከድር ለብስራት ሬዲዮ  ተናግረዋል።
ፖሊስ ግለሰቡ በተጠረጠረበት የግብረ ስጋ ድፍረት በደል መፈፀም ወንጀል የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ህግ ያስተላልፋል፡፡
ተከሳሽ ወንጀሉን አልፈፀምኩም ብሎ ክዶ የተከራከረ ሲሆን ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ ከሰማ በኃላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የቀረበበትን የወንጀል ክስና ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ በተከሰሰበት የወንጀል ህግ ጥፋተኛ ተብሏል ።
በዚህም የሀላባ ቁሊቶ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት  ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ክስ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፉን ኮማንደር ኑርዬ ከድር  ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ  ተናግረዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: