የባህር ዳር ስታዲየም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ጊዜያዊ ፈቃድ አገኘ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I I የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በቅርቡ በባህር ዳር ስታዲየም ላይ ያደረገውን ፍተሻ እና ግምገማ ተከተሎ ብሄራዊ ቡድናችን በመስከረም ወር 2019 በሜዳው ለሚያደርገው ጨዋታ የሚያገለግል ጊዜያዊ የካቴጎሪ 3 (CAT 3) ፈቃድ መስጠቱን ዛሬ ለኢ/እ/ፌ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል። ይህ ጊዜያዊ ፈቃድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚጠብቀውን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሜዳው ጨዋታን በሀገሩ እንዲያደርግ ያስችለዋል።

ካፍ በስታዲየሙ የተመዘገቡ መሻሻሎችን በማድነቅ በላከው ደብዳቤ አሁንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጿል። የተቆጣጣሪ ቡድኑን ግኝቶችና የሚቀሩ የማስተካከያ እርምጃዎችን የያዘ ሙሉ ቴክኒካዊ ሪፖርት በቅርቡ ለፌዴሬሽኑ እንደሚላክ ገልፆ ጨዋታው በሚደረግበት ቀን የስታዲየሙን ዝግጁነት እና የደንቦች አተገባበር ለመከታተል የስታዲየም ተቆጣጣሪ ሊመድብ እንደሚችልም አስታውቋል።

Via: ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: