#Ethiopia | ባየርን ሙኒክ እና አርቢ ላይፕዚግ ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ጀማል ሙስሌያ በጨዋታው 84ኛ ደቂቃ ላይ ራሱን ስቶ ሜዳ ላይ ወድቋል።
ባየርን ሙኒክ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አርቢ ላይፕዚግን ባሸነፈበት የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ሙስሌያ የቡድኑን 3ኛ ግብ አስቆጥሮ ነበር።
በዕለቱ በነበረው ጨዋታ ተጫዋቹ የደም ዝውውር ችግር አጋጥሞት ሜዳ ላይ እራሱን ስቶ እንደወደቀ ተገልጿል።
ዳኛው ጨዋታውን ወዲያውኑ ያስቆሙ ሲሆን የድንገተኛ ህክምና ሀኪሞች ቡድን ወደ ሜዳ ገብተው አስቸኳይ እርዳታ አድርገውለታል ተብሏል።
ተጫዋቹ የህክምና ክትትል ተደርጎለት ለተጨማሪ ህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ነው የተገለፀው።
ተጫዋቹ የደረሰበት የህክምና ችግር ለክፋት የሚሰጥ እንዳልሆነ የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#BayrenMunch #Leipzig
#Friendlymatch #football
Source: GetuTemesgen









No comments yet.