ካፍ ዋልያዎቹ በባህርዳር ስታዲየም እንዲጫወቱ ፍቃድ ሰጠ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) ለባህር ዳር ስታዲየም የጊዜያዊ ‘ካቴጎሪ 3’ እውቅና መስጠቱን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጪውን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በሀገሩ ማስተናገድ እንደሚችል ተረጋገጠ።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው በስታዲየሙ ላይ በርካታ የማሻሻያ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላ ሲሆን ካፍ የተደረጉትን አዎንታዊ ለውጦች ቢቀበልም ገና ትኩረት የሚሹ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውንም አመልክቷል።

​ይህ ጊዜያዊ ፈቃድ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ ብስራት ሲሆን ብሔራዊ ቡድኑ ከአምስት ዓመታት ረጅም ጥበቃ በኋላ በገዛ ሀገሩ እና በደጋፊዎቹ ፊት የዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ለማድረግ ያስችለዋል።

ከዚህ ቀደም ከስታዲየሙ መሰረተ ልማት ጋር ተያይዘው ይነሱ የነበሩ ነቀፋዎች ሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን በገዛ ሜዳዋ እንዳታስተናግድ አግደዋት የቆዩ ቢሆንም የአሁኑ ውሳኔ ለዋልያዎቹ የሜዳ ላይ ደጋፊን የመጠቀም ትልቅ እድልን ይዞ መጥቷል።

​ሆኖም የተሰጠው እውቅና ጊዜያዊ በመሆኑ ስታዲየሙ የካፍን ሙሉ መስፈርት አሟልቶ እንዲቀጥል ተጨማሪ የማሻሻያ ስራዎች እንደሚቀሩ ተገልጻል።

ብሔራዊ ቡድኑም የሜዳውን እድል በመጠቀም ወደ አህጉራዊው ውድድር ለማለፍ የሚያደርገውን ጉዞ ያጎለብትለታል ተብሎ ይታመናል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

​#GetuTemesgen #Walias #CAF #EthiopianFootball #BahirDarStadium #AFCON2027


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: