*ስታዲየም ዙሪያ በፔናሊቲ የዋንጫው ባለቤት ሆነ
#Ethiopia | በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቤላ ስፖርት ጋር በመተባበር ለተከታታይ አንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድር በስታዲየም ዙሪያ ክለብ አሸናፊነት በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።
በጨፌ ሜዳ በተካሄደው የመጨረሻ የፍጻሜ ግጥሚያ ስታዲየም ዙሪያ ከሽሮ ሜዳ ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 ተጠናቋል።
በመቀጠል በተሰጠው መለያ ምት ስታዲየም ዙሪያ 5 ለ 4 በሆነ አሸናፊነት የውድድሩን ዋንጫ እና የ1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት አሸንፏል።
ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድር 24 ክለቦች የተሳተፉበት ሲሆን በውድድሩ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ፣ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣ ኢንትራክተር አብርሃም መብራቱ እና የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ተገኝተው ጨዋታውን ታድመዋል።
#AddisAbabaFootball #EthiopianFootball
#AddisAbabaSport #WinterTournament
#Champions



Source: GetuTemesgen








No comments yet.