‎የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድር ተጠናቀቀ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎*ስታዲየም ዙሪያ በፔናሊቲ የዋንጫው ባለቤት ሆነ

‎#Ethiopia | ​በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከቤላ ስፖርት ጋር በመተባበር ለተከታታይ አንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድር በስታዲየም ዙሪያ ክለብ አሸናፊነት በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

‎​በጨፌ ሜዳ በተካሄደው የመጨረሻ የፍጻሜ ግጥሚያ ስታዲየም ዙሪያ ከሽሮ ሜዳ ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 ተጠናቋል።

‎በመቀጠል በተሰጠው መለያ ምት ስታዲየም ዙሪያ 5 ለ 4 በሆነ አሸናፊነት የውድድሩን ዋንጫ እና የ1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት አሸንፏል።

‎ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ የክረምት እግር ኳስ ውድድር 24 ክለቦች የተሳተፉበት ሲሆን በውድድሩ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃይለጊዮርጊስ ፣ ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣ ኢንትራክተር አብርሃም መብራቱ እና የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ተገኝተው ጨዋታውን ታድመዋል።

‎#AddisAbabaFootball ​#EthiopianFootball
​#AddisAbabaSport ​#WinterTournament
​#Champions






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1