ማን ያሸንፋል?!

- Advertisement -
Sidebar AD

አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ለኮሚኒቲ ሺልድ ክብር ይፋለማሉ

#Ethiopia | የእንግሊዝ የእግር ኳስ የውድድር ዘመን መክፈቻ የሆነው የኮሚኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል።

ይህ ውድድር የፕሪሚየር ሊግ እና የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊዎችን የሚያገናኝ ሲሆን አንድ ክለብ ሁለቱንም ዋንጫዎች ካነሳ በሊጉ ሁለተኛ የወጣው ቡድን ይሳተፋል።

በዚህ መሠረት የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ አርሰናል የኤፍ ኤ ካፕ ባለድሉን ማንችስተር ሲቲን የሚገጥም ይሆናል።

ይህ ጨዋታ የዋንጫ ፍልሚያ ቢሆንም በእንግሊዝ እግር ኳስ የሚሰጠው ግምት አነስተኛ ነው። አንዳንዶች እንደ ጠንካራ የወዳጅነት ጨዋታ የሚቆጥሩት ሲሆን ዋንጫውም እንደ ዋና ዋና ውድድሮች አይታሰብም። ይህም ሆኖ ክለቦች ዋንጫውን ለማንሳት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

ዛሬ አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ በ104ኛው የኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ የሚያደርጉት ፍልሚያ ዋና ዓላማ ጋሻ መሰሉን ዋንጫ ማሸነፍ ነው።

ከ22 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በማንሳት ለዚህ ጨዋታ የበቃው አርሰናል የኮሚኒቲ ሺልድን 17 ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ በዚህ ዘርፍ የሚበለጠው 21 ጊዜ ካሸነፈው ማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ነው። መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ ይህን ዋንጫ ያነሱት ማንችስተር ሲቲን በመለያ ምት በማሸነፍ ነበር።

በሌላ በኩል ማንችስተር ሲቲ ዋንጫውን ሰባት ጊዜ ያነሰ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ያሸነፈው በ2024 ማንችስተር ዩናይትድን በመለያ ምት አሸንፎ እንደነበር ይታወሳል።

በዛሬው ጨዋታ በአርሰናል በኩል ቡካዮ ሳካ፣ ዴክላን ራይስ፣ ማርቲን ዙቢሜንዲ እና አዲሱ ፈራሚ ብሩኖ ጊማሬሽ ይሰለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በማንችስተር ሲቲ በኩል ደግሞ ኧርሊንግ ሀላንድ እና አዲሱ ፈራሚ ኤሊዮት አንደርሰን የመጫወት ዕድል ያላቸው ሲሆን አማካዩ ሮድሪ ግን ይሰለፋል ተብሎ አይጠበቅም።

በካርዲፍ ሚሊኒየም ስታዲየም የሚካሄደው ይህ ጨዋታ ምሽት 11:00 ሰዓት ላይ ይጀምራል።

#arsenal #mancity #communityshield #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1