በይቅርታ መንገድ በፍቅር እንራመድ

- Advertisement -
Sidebar AD

“ታይላ ጥላቻን በፍቅር መለሰች”

#Ethiopia | ደቡብ አፍሪካዊቷ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኮከብ ታይላ (Tyla) በቅርቡ በታላቅ ድምቀት በተካሄደው የሽልማት መድረክ ላይ ያሳየችው አቋም የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

ታይላ የዓለም አቀፍ ስኬት አሸናፊ በመሆን የክብሩ ባለቤት በሆነችበት ወቅት የራሷን ስኬት ብቻ ከማክበር ይልቅ የመድረኩን ትኩረት ወደ አህጉራዊ አንድነት አዞራዋለች።

በቅርቡ በናይጄሪያ እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ከተፈጠረው ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ውጥረት ጋር ተያይዞ በሌጎስ ልታደርገው ያሰበችውን ኮንሰርት እንድትሰርዝ ተፅዕኖ ተደርጎባት ኮንሰርቷን መሰረዟ ይታወሳል።

የቀረበባትን ቅሬታ እና ጥላቻ ግን በጥላቻ ሳይሆን የመለሰችው በበሰለ አቀራረብ እና በፍቅር መመለስን ነበር የመረጠችው።

በሽልማት በስነ ስርዓቱ ላይ የታደሙትን አፍሪካውያን አርቲስቶች በሙሉ ወደ መድረክ እንዲወጡ በመጋበዝ የደስታዋ አካል አድርጋቸዋለች።

የደቡብ አፍሪካዊቷ የሙዚቃ ኮከብ ታይላ በሌጎስ ልታደርገው የነበረው ኮንሰርት መታገዱን እና ከተፈጠሩ ውጥረቶች በኋላ በሽልማት መድረክ ላይ ያሳየችው ተግባር ከብዙዎች አክብሮት አትርፎላታል።

ደቡብ አፍሪካዊቷ ታዋቂ የሙዚቃ ኮከብ ታይላ በቅርቡ በተዘጋጀውና ባሸኘፈችው የሽልማት መድረክ በመጠቀም በአፍሪካውያን ድምፃውያን መካከል ጠንካራ አንድነት እንዲኖር ጥሪ አቅርባለች።

ይህ ድርጊቷም በአፍሪካ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን አብሮነት እና አህጉራዊ አንድነት ያሳየ ትልቅ ክስተት ተብሏል።

ይህም በኪነ ጥበብ በኩል አህጉራዊ ትስስርን እንደገና ለመገንባት የተደረገ አዎንታዊ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Tayla #southafrica #music
#Nigeria #entertainment


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2