በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከገነኑ መላእክት ከቅዱስ ሚካኤል ቀጥሎ የሚጠራው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ መልአኩ ገብርኤል በቅድስናው ቅዱስ ይባላል፡፡ የዙፋን መልእክተኛ ነውና መልአክ ወይም መልእክተኛ ይባላል፡፡ የሠራዊት አዛዥ ነውና ሊቀ መላእክት ይባላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል አብሳሬ ትስብዕት ነው፡፡ እመቤታችን አምላክን እንደምትወልድ ታላቁን የምሥራች ይዞ የደረሰው እርሱ ነው፡፡ የሰው ልጆችን መዳን ታላቁን የምሥራች ይዞ በመምጣቱና በሀዲስ ኪዳን ስሙ ተደጋግሞ በመጠቀሱ መጋቤ ሐዲስ ይባላል፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የተሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ነው፡፡ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ መጥምቁ ዮሐንስን እንደሚወልድ የዘመናትን የጸሎት ምላሽ ይዞ የመጣ፣ በባቢሎን ምርኮ ሆኖ ስለሕዝቡ የሚያለቅሰውን የነቢዩ ዳንኤልን የጸሎት መልስ ይዞ የመጣው፣ ራእዩንም ያብራራለት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ይህም ደግሞ እውነት ነው፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል።
በዕምነታቸው የጸኑት ሦስቱ የባቢሎን ሕጻናት አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” አሉት፡፡ ወደ እቶን እሳት ተጣሉ፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው፡፡ ናቡከደነጾርም ተደንቆ በእሳቱ ላይ ሦስት ሰዎች ሰዎች ጥለን ነበር አሁን ግን አራት ሰዎች አያለሁ፤ የአራተኛውም መልክ የአምላክን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ይህ የአምላክን መልክ ይመስላ የተባለው ቅዱስ ገብርኤልን ገዳማውያን በመንፈሳዊ ውጊያቸው ሁሉ ይረዳቸዋል፡፡ የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንድንሆን በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Source: Yeneta Tube









No comments yet.