#Ethiopia | በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ ዋራ በተባለ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጠ።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር መለሰ ቡኑራ እንዳስታወቁት አደጋው የተከሰተው ትላንት ምሽት አንድ ሰአት ተခွဲ አካባቢ ነው። ከአለታ ወንዶ ወደ ሐዋሳ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ከሐዋሳ ወደ አለታ ወንዶ ተሳፋሪዎችን አጭኖ ሲጓዝ ከነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
ከዚሁ አደጋ ጋር ተያይዞ አደጋውን ለማየት ቆመው በነበሩ ተሽከርካሪዎች መካከል በተከሰተ ተጨማሪ የሲኖትራክ ግጭት ሌላ ተጨማሪ ጉዳት ደርሷል።
በመጀመሪያው አደጋ የኣንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሁለተኛው ግጭት ደግሞ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በአደጋው የሁለት ሴቶች እና የአንድ ወንድ ህይወት ያለፈ ሲሆን በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በአንድ ሰው ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በጤና ተቋማት የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። የክልሉ ፖሊስ ለአደጋው መንስኤ የሆነውን ሁኔታ በተቀናጀ ቡድን እየመረመረ እንደሚገኝ አስታውቋል።
#sidamaregion #trafficaccident #sidamazone #ethiopianews
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.