ኮሜዲያን ያሲኖ የ”ቤተሰብ ጨዋታ” አቅራቢ ሆኖ ተመረጠ
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ለረጅም ጊዜ በስክሪን ላይ የቆየውንና በብዙዎች ዘንድ የሚወደደውን “ቤተሰብ ጨዋታ” ዝግጅት በዋና አቅራቢነት እንዲመራ ኮሜዲያን ያሲኖን በተመልካቾች መረጠ።
የዝግጅቱ የረጅም ጊዜ አቅራቢ የነበረው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ተከትሎ ኢቢኤስ አዲስ አቅራቢ ለመተካት በተለያዩ አርቲስቶች እና ኮሜዲያኖች መካከል አቅም የመለካት ውድድር ሲያካሂድ ቆይቷል።
ተወዳዳሪዎቹ በስቱዲዮ ውስጥ ባሳዩት የዝግጅት አቀራረብ ብቃት እና ከተመልካች በተሰበሰበ የኤስኤምኤስ (SMS) ድምጽ መሰረት ኮሜዲያን ያሲኖ ከመጨረሻዎቹ አራት እጩዎች መካከል በከፍተኛ የድምጽ ልዩነት ማሸነፉ ተረጋግጧል።
አሸናፊነቱን ተከትሎም በየሳምንቱ ፕሮግራሙን በዋና አዘጋጅነት የመምራት ኃላፊነቱን ተረክቧል።
ውጤቱ ይፋ ከተደረገ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ኮሜዲያን ያሲኖ ያለፈበትን አስቸጋሪ የህይወት ጉዞ በማስታወስ ለተመልካቾች መልዕክት አስተላልፏል።
ለሰባት ዓመታት ያህል በመስተንግዶ እንዲሁም በታክሲ ረዳትነት ሲሰራ እንደነበርና የራሱ ሞባይል ስልክ እንኳን ሳይኖረው በሰው ስልክ ቪዲዮዎችን እየቀረፀ የቲክቶክ ተከታዮቹን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ማድረስ እንደቻለ ገልጿል።
ኢቢኤስ ቴሌቪዥንም የ”ቤተሰብ ጨዋታ” ዝግጅት የሚቀርብበትን ስቱዲዮ ሙሉ በሙሉ ውብ በሆነ የውስጥ ዲዛይን በማደስ ለአዲሱ ምዕራፍ ዝግጁ ማድረጉ ታውቋል።
አዲሱ አዘጋጅ ኮሜዲያን ያሲኖም የነጻነት ወርቅነህን አደራ በመረከብ ፕሮግራሙን አዝናኝና ሳቢ አድርጎ ለተመልካች ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጻል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.