#NewsAlertአብን፣ በምክክር ጉባኤው የታየው ግድፈት “ከተራ የአሠራር ግድፈት” ወይም “ከመደበኛ የፓለቲካ ልዩነት” የዘለለ…

- Advertisement -
Sidebar AD
#NewsAlert
አብን፣ በምክክር ጉባኤው የታየው ግድፈት “ከተራ የአሠራር ግድፈት” ወይም “ከመደበኛ የፓለቲካ ልዩነት” የዘለለ ነው አለ።
ፓርቲው፣ የምክክሩን “ተዓማኒነት”፣ “አካታችነት”፣ “ገለልተኝነት” እና “ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ “ተደጋጋሚ” እና “የተደራጁ “ጥፋቶች ተፈጽመዋል በማለት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ተችቷል።
በምክክሩ የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ድምጽና ፍላጎት ባግባቡ ሳይወከልና እንደ ዋና ባለቤት ሳይቆጠር መታለፉ “እጅግ አሳሳቢ” ነው ያለው ፓርቲው፣ የከተማዋ ተወካዮች የአንድን ወገን “ያልተገራ” እና “ድንበር የለሽ” ፍላጎት ለማስፈጸም ሲሉ የነዋሪዎችን መብትና ጥቅም አሳልፈው ሠጥተዋል በማለት ወቅሷል።
ፓርቲው በምክክሩ ላይ የታዩ ጥሠቶች ካልታረሙ፣ ለውጤቱ ፈጽሞ እውቅና እንደማይሠጥና እንደማይተባበር አስታውቋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: