#Ethiopia | የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በክልሉ የፖሊስ ተቋም ከፍተኛ አመራር ላይ አዲስ ሹመት አድርገዋል።
በዚህም መሠረት ሌተናል ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሆነው ተሾመዋል።
በሌላ በኩል ተቋሙን በዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥነት ሲመሩ የቆዩት ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶክተር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለሁለቱም ተሾሚዎች በስራ ዘመናቸው ስኬትንና መልካም የስራ ጊዜ ተመኝቷል።
#የአማራክልል #አረጋከበደ #ሹመት #የፖሊስአመራር #ፌደራልፖሊስ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.