ለፈተና 4.5 ኪሎ ሜትር በከባድ የበረዶ ግርግር ተጓዞ 99 ያመጣው የ8 ዓመቱ ህጻን!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቻይና ገጠራማዋ አካባቢ የሚኖረው የ8 ዓመቱ ህጻን ዋንግ ፉማን ለፈተና ለመድረስ ሲል በከባድ ቅዝቃዜ ውስጥ ያደረገው ረጅም ጉዞ የመላውን ዓለም ትኩረት ስቧል።

ህጻኑ በዚያ የፈተና ቀን ከዜሮ በታች በሆነ ቅዝቃዜ ውስጥ 4.5 ኪሎ ሜትር በእግር ተጉዞ ትምህርት ቤት ደርሷል።

ህጻኑ ትምህርት ቤት ሲደርስ ፀጉሩ ቅንድቡ እና የዓይን ሽፋሽፍቶቹ ሙሉ በሙሉ በበረዶ ተሸፍነው ነበር።

እንዲሁም እጆቹም በቅዝቃዜው ምክንያት ቀልተውና አብጠው ነበር ተብሏል።

ዋንግ ይህን ሁሉ አስቸጋሪ መንገድና ከባዱን ቅዝቃዜ ተቋቁሞ በማለፍ በተፈተነው ፈተና 99 ከ 100 ማምጣት ችሏል።

የህጻኑ ታሪክ በገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ ህጻናት የሚያጋጥሟቸውን ችግር አጉልቶ ያሳየ ሲሆን የብዙዎችን ልብ በመንካቱ ለህጻኑ እና ለትምህርት ቤቱ አልባሳት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ እየጎረፉ ይገኛል ነው የተባለው።

ዋንግ ፉማን በአንድ የበረዶ ግርግር አማካኝነት ዓለም አቀፍ እውቅናን ያገኘ ቢሆንም ለትምህርት ባለው የማይናወጥ ጽናት እና ጥንካሬ አድናቆት እንዲያገኝ አድርጎታል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#China #schools #students
#Ice #Coldest #exams
#IceBoy #WangFuman


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: