መንግስት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሞብናል ሲል ሕወሃት ከሰሰ። የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት መቀሌ ከተማ አ…

- Advertisement -
Sidebar AD
መንግስት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሞብናል ሲል ሕወሃት ከሰሰ።
የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሞብናል ሲሉ ሕወሃት መራሹ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ከሰዋል።
የባለስልጣናቱ ክስ የተሰማው በሁለቱ ኃይላት መካከል ከዛሬ ነገ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለው ውጥረት እያየለ በመጣበት ወቅት ነው።
የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉን ከላሊ ሃጋዚን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው የፌደራል ኃይሎች ከክልሉ መዲና መቀሌ በግምት 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዳንደራ በተባለች መንደር ውስጥ ባለ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማእከል ላይ ጠዋት 4:00 ገደማ “የድሮን ጥቃት ፈፅመዋል” ብለዋል።
ደረሰ በተባለው የድሮን ጥቃት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጹት ባለስልጣኑ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዳልሰጡ ዘገባው አመልክቷል።
አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ካህን ግን በጥቃቱ ቢያንስ አንድ ሰው መገደሉን ተናግረዋል።
በድሮን ጥቃቱ የተወነጨፈው ሚሳኤል በአንድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ መውደቁን መመልከታቸውን የተናገሩት ካህኑ ለዜና ወኪሉ “በጥቃቱ የተገደለ አንድ ታጣቂ በቁስለኛ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ሲወሰድ አይቻለሁ” ብለዋል።
በህወሃት እና በፌዴራል መንግስቱ መካከል ዳግም ጦርነት ቀስቃሽ ውጥረት ከተከሰተ ወዲህ የድሮን ጥቃት ሲፈጸም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይህ ሁለተኛው ነው።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1