#Ethiopia | በኮሎምቢያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የተጎዱ አካባቢዎችን ለመደገፍ ድምፃዊት ሻኪራ እርዳታ ሰጠች።
ኮሎምቢያዊት ድምፃዊት ሻኪራ በአገሯ አሰቃቂ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ወደ ተከሰተበት ቾኮ ክልል በመጓዝ የተጎዱ አካባቢዎችን ጎብኝታለች።
ሻኪራ ከተለያዩ ባለሀብቶች ጋር በመሆን በዋና ከተማዋ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ተዘዋውራ ተመልክታለች።
በጉብኝቷ ወቅት ሻኪራ በአደጋው የወደሙ 10 አዳዲስ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እና የቾኮ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን መልሶ ለመገንባት ቃል ገብታለች።
ለአካባቢው መልሶ ግንባታ የሚሆን የመነሻ 1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቧም ይፋ አድርጋለች።
የአካባቢው ማህበረሰብ እና ህፃናት እንዳይረሱ ጥሪዋን አስተላልፋለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#heartattack #flight
#Colombia #shakira #earthquake #accident
Source: GetuTemesgen







No comments yet.