በሮም የክብር ሽልማት የተበረከተለትና ምስጋና የወረደለት ኢንስትራክተር

- Advertisement -
Sidebar AD

🔴

🔴”ለሀገሬ ያበረከትኩትን ውለታ አስታውሠው ለዚህ ክብር ያበቁኝን፣ዕድሉን የሠጡኝን በሙሉ ከልብ አመሠግናለሁ”

ኢንስትራክተር ካሣሁን ተካ

#Ethiopia | በጣሊያን ሮም ከተማ በተካሄደው 21ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ላይ በክብር እንግድነት የተጋበዙት አንጋፋው የስፖርት ባለሙያ ኢንስትራክተር ካሳሁን ተካ ከፍተኛ አክብሮትና የሽልማት እውቅና ተበረከተላቸው።

ከሐምሌ 20 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ዓመታዊ መድረክ ላይ በይፋ የተገኙት ኢንስትራክተሩ፣ ለሀገራቸው የስፖርት እድገት ላበረከቱት ዘመናትን የተሻገረ አስተዋጽኦ ለተሰጣቸው ክብር የተሰማቸውን ጥልቅ ደስታ ገልጸዋል።

በተጫዋችነት፣ በአሰልጣኝነት፣ በኢንስትራክተርነት እና በፌዴሬሽን አመራርነት ከ50 ዓመታት በላይ አገልግሎት የሰጡት ኢንስትራክተር ካሳሁን፣ ለሀገር የተዋለ ውለታ ተሰብሮ እና ታስቦ ለዚህ መሰል እውቅና መብቃት ትልቅ እርካታን እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

የአውሮፓው ፌስቲቫል ታዳጊዎችንና ህጻናትን ያቀፉ ውድድሮችን ማካተቱ በበጎ ጎኑ ሊነሳ የሚገባውና ከሌሎች መሰል መድረኮች የሚለየው ትልቅ እሴት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።

በቆይታቸው ወቅት የቀድሞ ደቀመዛሙርቶቻቸውን፣ ታዋቂ ተጫዋቾችንና የስፖርት አድናቂዎችን በአንድ ላይ ማግኘታቸው የስሜት እና የትዝታ ትስስር እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

በተለይም በአዲስ ብስራት የሚመራው የአውሮፓ የቀድሞ ተጫዋቾች ማህበር ባዘጋጀላቸው የክብር እራትና የሽልማት ስነ-ስርዓት፣ እንዲሁም አዲስ ብስራት፣ ሽመልስ ሊዮኔ፣ መስፍን ሊዮኔ እና የቀድሞ ግብጠባቂ አንድነት (ቀዮ) ላደረጉላቸው ሞቅ ያለ አቀባበልና እንክብካቤ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል፣ በፌስቲቫሉ ወቅት የተስተዋሉ አላስፈላጊ ውዝግቦችና ተቋማዊ ገጽታን የሚያጎድፉ ክስተቶች እንዳሳዘኗቸው አልሸሸጉም።

ችግሮች ቢኖሩ እንኳ በውይይት መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ ያሳሰቡት ኢንስትራክተሩ፣ አጠቃላይ መድረኩ ለሀገር የሰራን ባለሙያ የሚያከብር ትውልድ መኖሩን ያረጋገጠበት እንደነበር ገልጸዋል።

✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

​#sports #ethiopiansport #rome #italy #football #instructorkasahun #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: