በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አራት ህፃናትን በሰላም የተገላገለችው እናት በሙሉ ጤንነት ወደ ቤቷ ተሸኘች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በሰላም አራት ህፃናትን በወሊድ ያገኘችው ወጣት እናት፣ በሆስፒታሉ የህክምና ቡድን ላለፉት ስምንት ቀናት ሲደረግላት የቆየውን የቅርብ ክትትልና እንክብካቤ አጠናቃ ከነሙሉ ጤንነታቸው ከልጆቿ ጋር ወደ ቤቷ መሸኘቷን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

​ይህች የ26 ዓመት ወጣት እናት ባለፈው ሳምንት በሰላም የተገላገለቻቸው አራቱም ጨቅላ ህፃናት በተወለዱበት ወቅት የነበራቸው ክብደት ከ1 ነጥብ 4 እስከ 1 ነጥብ 9 ኪሎ ግራም የነበረ በመሆኑ፣ ወዲያውኑ በጨቅላ ህፃናት ማጠናከሪያ ክፍል (NICU) ውስጥ በማሞቂያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል። ባለሙያዎቹ ባደረጉላቸው ከፍተኛ የህክምና እና የነርሲንግ ክትትልም የህፃናቱ እና የእናትየው ጤንነት በፍጥነት ወደ ሙሉ መልካም ሁኔታ ሊመለስ ችሏል።

​የጤና ባለሙያዎቹ ባደረጉት የተቀናጀና ስኬታማ የቅርብ ክትትል ምክንያት አራቱም ህፃናትና እናታቸው በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ መሆናቸው በመረጋገጡ፣ ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የሆስፒታሉን ቆይታቸውን አጠናቀው በደስታ ወደ ቤታቸው እንዲሸኙ ተደርጓል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2