ንፁህ የመጠጥ ውሃ ከሚያገኙ ሰዎች ይልቅ ስማርት ስልክ ያላቸው ሰዎች ቁጥር ይበልጣል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአለም የጤና ድርጅት በዓለም ላይ ወደ 2 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ማለትም ከዓለም ህዝብ 26 በመቶ የሚሆኑት ንፁህ የመጠጥ ውሃ አያገኙም ብሏል።

ድርጅቱ በበርካታ ታዳጊ ሀገራት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ከሚያገኙ ሰዎች ይልቅ በእጃቸው ስማርት ስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ያላቸው ሰዎች ቁጥር ይበልጣል ነው ያለው።

በአለም አቀፍ ደረጃ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በታዳጊ ሀገራት ንጹህ የመጠጥ ውሀ ችግር አሁንም አልተቀረፈም ሲል ገልጿል።

አብዛኛው የዓለም ህዝብ አስተማማኝ የመጠጥ ውሃ የሚያገኝ ቢሆንም አሁንም 2 ቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በውሃ ምክንያት ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው ሲል የአለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

በአለም አቀፍ ደረጃ በግምት 74 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ወደ 6 ቢሊዮን ሰዎች በአቅራቢያቸው ደህንነቱ የተጠበቀ እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ ያገኛሉ ብሏል።

በተጨማሪም 18 በመቶ የሚሆነው ህዝብ መሰረታዊ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚያገኙች ከ30 ደቂቃ በላይ ተጉዘው ነው ሲል ጥናቱ ያመላከተው።

ወደ 115 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ያልተጣራ እና ክፍት የሆኑ ወንዞች ሐይቆች እና ኩሬዎችን ለመጠጥነት እንደሚጠቀሙ ነው የተገለፀው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Un #water #scarcity
#Disease #wateraid
#Developingnation


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2