የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የ20,000 ችግኝ ተከላ ዕቅዱን አጠናቀቀ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:-የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከ500 በላይ ወጣቶች እና ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት በሸገር ከተማ በገፈርሳ ጉጄ አካባቢ 9,000 ችግኞችን በመትከል የዓመቱን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በይፋ አጠናቀቀ።

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ በሰባቱም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶቹ እና በተለያዩ ክልሎች አማካኝነት ከ20,000 በላይ ችግኞችን ለመትከል አቅዶ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ የዛሬው መርሃ ግብር የዚሁ ሀገራዊና ተቋማዊ የልማት ጥረት አካል መሆኑ ተገልጻል።

ከተተከሉት ችግኞች መካከል 60 በመቶ ያህሉ የፍራፍሬ ችግኞች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 40 በመቶ ደግሞ ሀገር በቀል ዛፎች መሆናቸዉ እንዲሁም የፍራፍሬ ችግኞች በስፋት እንዲተከሉ የተደረገበት ዋና ምክንያት የአካባቢ ጥበቃን ከምግብ ዋስትና ጋር ለማስተሳሰር መሆኑን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሄራን ገርባ ገልጸዋል።

ወ/ሮ ሄራን አክለዉም ምርቱ ማህበረሰቡ አስፈላጊ የሆኑ የቫይታሚንና የንጥረ ነገሮች ምንጭ የሆኑ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በበቂ ሁኔታ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በላይ፣ አጠቃላይ የአመጋገብ ስርዓትንና ባህልን በመቀየር በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነዉ የተገለፀዉ።

በዛሬዉ ችግኝ ተከላ ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የስልጠና እና የተፈጥሮ እንክብካቤ በችግኝ ተከላው የተሳተፉት ወጣቶች የተፈጥሮ ሀብትን ከመንከባከብ ባለፈ፣ በጤናቸውና በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ አደንዛዥ ዕፆች፣ ከትምባሆ እና ከአልኮል ሱሰኝነት ራሳቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል የሶስት ዙር ስልጠና የተሰጣቸው መሆኑ ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የተተከሉት ችግኞች ተንከባካቢ አጥተው እንዳይደቁ ለማድረግ ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ከወጣቶቹ እና ከሰራተኞቹ ጋር በመቀናጀት ዘላቂ የመከታተያና የእንክብካቤ ፕሮግራም ዘርግቶ እንደሚሰራ አረጋግጧል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: