#Ethiopia | ለሰዓታት የአለማችን ቁጥር አንድ ባለዕዳ የነበረችው አሜሪካዊት ወጣት አስገራሚ አጋጣሚ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል።
ነገሩ እንዲህ ነው…
ማዲ ማክጊቨርን የተባለችው አሜሪካዊት ወጣት ከጓደኞቿ ጋር በመጠጥ ቤት ጥሩ ምሽት አሳልፋ ወደ ቤቷ ትመለሳለች።
አልጋዋ ላይ ከማረፏ በፊት ግን እስኪ ዛሬ ምሽት ስንት አወጣሁ? ብላ የባንክ አካውንቷን በስልኳ መተግበሪያ ልታይ ከፈተች።
ይሁን እንጂ በስክሪኑ ላይ ያየችው ቁጥር በህይወቷ አይታው አታውቅም።
ማዲ ሁኔታውን ስታስታውስ እንዲህ ትላለች በጠጣሁት መጠጥ ሳልሰክር ያየሁት ቁጥር አሰከረኝ አሜሪካ በግሌ የገዛኋት ነው የመሰለኝ ስትል ሁኔታውን ተናግራለች።
በእኩለ ሌሊት በፍርሃት ተውጣ ወደ ባንኩ የደንበኞች አገልግሎት ደውላ
የደወልኩት የ50 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ለመክፈል ሳይሆን እንዴት ይሄ ሊሆን እንደቻለ ልጠይቅ ነው አለች።
ስልኩን ያነሳው የባንኩ ሰራተኛም በስክሪኑ ላይ ያየውን ቁጥር ማመን አቅቶት ለሰከንዶች ዝምታ ሰፍኖ እንደነበር ገልጻለች።
ለጥቂት ሰዓታት ያህል ከጓደኞቿ ጋር አምሽታ በመመለሷ ብቻ የ50 ቢሊዮን የአለማችን ቁጥር 1 ባለዕዳ ሆና አምሽታለች።
በኋላ ላይ ቼዝ ባንክ በሰጠው መግለጫ በሲስተሙ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት በጥቂት ደንበኞች ላይ የተሳሳተ ቁጥር መዝግቧል ሲል ገልጿል።
በመጨረሻም ባንኩ የወጣቷ 50 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሰርዞ ትክክለኛውን ሂሳቧን አስቀምጦላታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#American #nightclubs
#Balance #accounts
#bank #technicalglitch
Source: GetuTemesgen








No comments yet.