#FastMereja I የሳውዲ አረቢያ የድንበር ጥበቃ ሃይል በጃዛን እና አሲር ክልሎች ባካሄዳቸው የተለያየ የቁጥጥር ኦፕሬሽኖች የድንበር ጥሰት የፈጸሙ 8 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል 124 ኪሎ ግራም ጫት እና 34 ኪሎ ግራም ሀሺሽ መያዙን አስታወቀ። የደህንነት ሃይሉ ህገ-ወጥ እፆቹ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ማክሸፉን ገልጾ፣ ከተያዙት ግለሰቦች መካከል የየመን እና የኢትዮጵያ ዜጎች እንደሚገኙበት አስታውቋል።
በጃዛን ክልል አል-አሪዳህ ሴክተር በተካሄደ የመጀመሪያ ዙር ፍተሻ 84 ኪሎ ግራም ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሲሞክሩ የነበሩ ስድስት የየመን ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተመሳሳይ በዚህ ባለው አል-አሪዳህ ሴክተር በተካሄደ ሌላ ተጨማሪ ኦፕሬሽን 34 ኪሎ ግራም ሀሺሽ ለማስገባት የተደረገው ሙከራ በድንበር ጥበቃ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል።
በሌላ በኩል በአሲር ክልል አል-ራቡአ ሴክተር በተካሄደ ተመሳሳይ የክትትል ስራ 40 ኪሎ ግራም ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት የኢትዮጵያ ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የሳውዲ አረቢያ የሚመለከታቸው ባለስልጣናት እንደገለጹት በቁጥጥር ስር በዋሉት ተጠራጣሪዎች እና በተያዙት እፆች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ህጋዊ ሂደቶች የተጠናቀቁ ሲሆን፣ ሁሉም ግለሰቦች እና የተያዙት እፆች ጉዳዩ ለሚመለከተው የህግ አካል ተልከዋል።
Source: FastMereja








No comments yet.