”በእረፍት ቀኔ መዝናናት አያምረኝም” የደሃዎች ወዳጅ ናሲር ሶብሃኒ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በሜልበርን ከተማ የሚኖረውና ከሱሰኝነት ተላቆ ወደ ሙሉ ጤንነቱ የተመለሰው የፀጉር አስተካካዩ ናሲር ሶብሃኒ የሙያ እውቀቱን በመጠቀም በከተማዋ የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎችን መልክ በመቀየር ላይ ይገኛል።

ከዛሬ 12 ዓመት ጀምሮ በሳምንት የዕረፍት ቀኖቹ የመቁረጫ መሣሪያዎቹንና ወንበሩን ይዞ በከተማዋ ጎዳናዎች በመዘዋወር የመኖሪያ ቤት አልባ ወገኖችን እየፈለገ ነፃ የፀጉር ቁርጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

​ለአንድ ሰው የሚሰጠው ከ20 እስከ 40 ደቂቃ የሚወስድ የፀጉር ቁርጥ አገልግሎት በሌሎች ዘንድ ትኩረት አጥተውና ተረስተው ለሚኖሩ ሰዎች የሰው ልጅ አክብሮትና ትኩረት የሚያገኙበት ድንቅ አጋጣሚ ሆኗል።

ናሲር በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ታሪካቸውን በትዕግሥት በማዳመጥና ሙሉ ትኩረቱን በመስጠት ሰብአዊ ክብራቸውን ያጎናፅፋቸዋል።

​ለእርሱ የዚህ በጎ አድራጎት ትልቁ ስኬት በፎቶግራፎች ላይ የሚታየው ውጫዊ ገጽታ መለወጥ ሳይሆን ሰው እንደሚያስብላቸውና ትኩረት እንደሰጣቸው ሲረዱ በውስጣቸው የሚፈጠረው አዎንታዊ የስሜት ለውጥ ነው።

ናሲር ሶብሃኒ የራሱን የፀጉር አስተካካይነት ንግድ እያካሄደ እንኳን በዕረፍት ቀኖቹ ወደ ጎዳና በመውጣት በጥቂት ደቂቃዎች የሰውዎችን ሕይወት በበጎ መልኩ መቀየር እንደሚቻል በተግባር እያሳየ ይገኛል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2