በወላይታ የዘመን አቆጣጠር ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በበዓሉ “Gifaata Gazzee Abuuna Gaylle” ተብሎ ይዘፈናል፡፡ ይህም የበዓሉን ታላቅነት ለመግለጽ ነው፡፡
ጊፋታ መቃረቡ ከሚገለጽበት መንገድ አንዱ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 30 የሚደርሱ ወጣቶች ለደመራ የሚሆን እንጨት የሚለቅሙበትና የሚያዘጋጁበት ወቅት ነው፤ ይህም የጉልያ ሥርዓት ይባላል።
የጊፋታ በዓል ከሌሎች በዓላት በተለየ የረዥም ወቅት ዝግጅት ይደረግለታል፡፡ ሁሉም የማህበረሰቡ አባላት ማለትም አባቶች፣ እናቶች እንዲሁም ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሕጻናትም ሳይቀሩ በጊፋታ በዓል ዝግጅት የየራሳቸው የሥራ ድርሻ አላቸው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የቅድመ ዝግጅት ሥራው በማህበር ወይም በደቦ ሆኖ አንዱ ሌላውን በማገዝም ይከናወናል፡፡ በጊፋታ ሁሉም የቤተሰብ አባላት የየራሳቸው የሥራ ድርሻ አላቸው፡፡
በጊፋታ በዓል ዝግጅት የወጣት ወንድ ልጆችና ልጃገረዶች ዋና ተግባር ወንዱ የጉሊያ እንጨት ከመቁረጥ፣ ከማቆምና ከማቃጠል እንዲሁም የማገዶ እንጨት ከመፍለጥ፣ የከብቶችን ሳር አጭዶ ከመከመር ውጪ በአጠቃላይ አባቱ በሚያደርገው እንቅስቃሴ አባቱን የሚረዳ ሲሆን ልጃገረዶችም በመጨረሻው ቀን እንሶስላ ከመሞቅ ውጪ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ እናታቸውን ያግዛሉ፡፡
ከዚህ በኃላ ጋዜ ኦሩዋ ”Gazze Oruwaa” ስደርስ አጠቃላይ ሀሳባቸውን ወደ መዝናኛ የሚያደርጉበት ነዉ፡፡ በዚህ የመንደሩ ወጣት ወንዶችና ወጣት ሴቶች በአካባቢው ታዋቂ ሽማግሌ ደጃፍ ተሰብስበው ወንዶች ሃያያ ሌኬ እያሉ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው ሎሚ ከልጃገረዶች በመለመን ለትዳር የሚፈልጓትን የሚመርጡበትና የሚያባብሉበት ሴቶችም ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ ምላሽ እየሰጡ የሚጫወቱት የጨዋታ ዓይነት ነው፡፡
በጋዚያ ወጣቶች ይዘፍናሉ፤ ትግል ይገጥማሉ፤ ሩጫ ይወዳደራሉ፤ የፈረስ ጉግስ ይደረጋል፤ ሎሚ ከልጃገረዶች ላይ ይለምናሉ፡፡
ልጃገረዶች አንድ ላይ በመሆን በየቡድኑ ተከፋፍለው ተቀምጠው “ሀያ ወላሎሜ” እያሉ ለወንዶች ሎሚ በመወርወር ይመርጣሉ፡፡
አንዳቸው ለሌላው ልዩ ሚስጥረኛ ይሆናሉ፤ ከዚያን ዕለት ጀምረው በስማቸው ሳይሆን የሚጠራሩት “ሎሜ ሎሜ” በማለት እርስ በርስ ይጠራራሉ፡፡
ሌላው ደግሞ ልጃገረዶች እርስ በርስ ለሚዜነት ከሚመርጧት ጋር አንድ ሎሚ በጥርሳቸው በጋራ በመካፈል እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ እርስ በርስ ሚስጥር በመጠበቅ የልብ ጓደኛሞች ይሆናሉ፡፡
በጋዚያ ቦታ ወላጆች የልጆቻቸውን ጨዋታ ለማየት አልፎ አልፎ ይመጣሉ፡፡ እርስ በርስ እንዳይጣሉና ግጭት እንዳይፈጠር እንዲሁም ደግሞ ጠለፋ እንዳይፈጸም ይከታተላሉ፡፡
በዚያ ቦታ ከጓደኞቻቸው ጋር በመገናኘት ”Booray Molshsha! Miizziyaa Oysso!“ በመባባል እርስ በራሳቸው ይጫወታሉ፤ በመጨረሻም አንድ ላይ ተቃቅፈው ለዘለዓለም እንኖራለን ”Merinaayyo Daana” በማለት አንዱ ለሌላው መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
#ዮዮ_ጊፋታ!!
#Yoo_Yoo_Gifaataa!
Source: FastMereja








No comments yet.