አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ለአዲሱ ተቋማዊ አርማ ውድድር አሸናፊውን ይፋ አደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ነባሩን የመለየቻ አርማ ወይም ሎጎ በአዲስ ለማሻሻል ያዘጋጀውን የንድፍ ውድድር አጠናቆ የአሸናፊውን ማንነት ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ ለአሸናፊው የሃምሳ ሺህ ብር ሽልማት ባዘጋጀበት በዚህ ውድድር ላይ መቶ ሰማንያ አራት የዘርፉ ባለሙያዎችና ፍላጎቱ ያላቸው ግለሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል።

አሸናፊውን ለመለየት የማኔጅመንት ኮሚቴው በርካታ ባለሙያዎችን ያማከረ ሲሆን፣ ምርጫውም ሳይንሳዊ መስፈርቶችንና የተቋሙን መሠረታዊ እሴቶች ባገናዘበ መልኩ ተካሂዷል።

በዚህም መሠረት የሆስፒታሉን ደረጃ ይመጥናል የተባለው አዲስ አርማ ተመርጦ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት ላይ እንዲውል ተደርጓል።

በውድድሩ ወቅት የቀረቡት ስራዎች የተመዘኑባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡

አንድ አርማ ሲዘጋጅ ከሦስት በላይ ቀለማትን መጠቀም ስለማይቻል ከዚህ ገደብ በላይ የተጠቀሙ ተወዳዳሪዎች ከውድድር ውጭ ሆነዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም ኤአይ በመጠቀም የተሰሩ ንድፎች ውድድሩ አይመለከታቸውም።

ቀሪዎቹ ስራዎች በቀላሉ የመረዳት እድል፣ የንድፉ ቀላልነት፣ አኒሜሽንና ሙሉ የብራንድ ትርጉም፣ ብቸኛነት፣ አእምሮ ውስጥ የመቀረጽ ብቃት፣ የአካባቢን ባህል የመግለጽ አቅም፣ ዘመናዊነት፣ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ላይ በሚገባ የመስተካከል ተለዋዋጭነት፣ የጽሁፍ ግልጽነት፣ ዘላቂነት እና ከተቋሙ እሴቶች ጋር ያለው ቁርኝት በተሰጡ ነጥቦች ተመዝነዋል።

ተቋሙ አያይዞም የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች አስተላልፏል፡

አንደኛ፣ ነባሩን የተቋሙን አርማ ሌሎች አካላት መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑ ተገልዟል።

ሁለተኛ፣ አሸናፊው አካል የስራውን ባለቤትነትና ትክክለኛነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ እንዲሁም የቴሌግራም ቁጥሩ ከኢትዮ ቴሌኮም የወጣበትን የቀበሌ መታወቂያ በአካል በመቅረብ ወይም በቴሌግራም በመላክ የሃምሳ ሺህ ብር ሽልማቱን መረከብ እንደሚችል ተገልጻል።

#AgewMidirHospital #LogoCompetition #BrandIdentity #HealthNews #EthiopianHealthcare #AgewMidir #HospitalLogo #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: