ዩቲዩብ የቪዲዮ እይታ አቆጣጠር መመሪያውን ቀየረዩቲዩብ የቪዲዮ እይታዎች የሚቆጠሩበትን መመሪያ ከነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ዩቲዩብ የቪዲዮ እይታ አቆጣጠር መመሪያውን ቀየረ
ዩቲዩብ የቪዲዮ እይታዎች የሚቆጠሩበትን መመሪያ ከነሐሴ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ መቀየሩን ይፋ አድርጓል። እስከዛሬ ድረስ አንድ ቪዲዮ «ታየ» ተብሎ እይታው የሚቆጠረው ተመልካቹ ቢያንስ ለ30 ሰከንዶች ያህል ሲመለከት ነበር።
በአዲሱ መመሪያ መሠረት ግን ቪዲዮው መጫወት እንደጀመረ በቀጥታ እንደ አንድ እይታ ተቆጥሮ የሚደመር ይሆናል ብሏል።
ይህ አዲስ አሰራር ዩቲዩብ አጫጭር ቪዲዮዎች ከሚቀርቡበት “Shorts” መድረክ ጋር አቆጣጠሩን አንድ ዓይነት ለማድረግና ወጥ አሰራር ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልጿል።
ይህ ለውጥ ይዘት አዘጋጆች የሚያገኙትን የቪዲዮ እይታ ቁጥር በጥቅሉ ሊጨምረው ቢችልም፣ የዩቲዩብ የገቢ ክፍያ እና ስፖንሰርሺፕ ግን አሁንም ተመልካቹ ቪዲዮውን ምን ያህል ሰዓት ተመለከተው (Watch Time) በሚለው መስፈርት ላይ ተመስርቶ እንደሚቀጥል ተብራርቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: