መቀሌ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ተመታች! የትግራይ ክልል ርዕሠ ከተማ መቀሌ ዛሬ ጠዋት በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መመታትዋን ህዝባዊ…

- Advertisement -
Sidebar AD
መቀሌ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ተመታች!
 
የትግራይ ክልል ርዕሠ ከተማ መቀሌ ዛሬ ጠዋት በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መመታትዋን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አስታወቀ።የትግራይ ክልልን የሚገዛዉ የህወሓት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ጥቃቱ ያነጣጠረዉ በሰዎች መኖሪያ አካባቢ ነዉ።የኢትዮጵያ የፌደራል መንግሥትና የህወሓት ጠብ እየተካረረ ነዉ።
ሁለቱ ኃይላት ትግራይን በሚያዋስኑ ድንበሮች ተጨማሪ ጦር ኃይል እያሰፈሩ መሆኑም ተዘግቧል።ባለፈዉ ማክሰኞ ከመቀሌ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሥፍራ በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መመታቱን የህወሓት ባለሥልጣናት አስታዉቀዉ ነበር።በጥቃቱ ቢያንስ አንድ ታጣቂ መገደሉና ሌሎች ሁለት መቁሰላቸዉን የዜና ምንጮች የጠቀሷቸዉ የአይን ምሥክሮች ተናግረዋል።
ዛሬ መቀሌ ዉስጥ በመኖሪያ ቤቶች አካባቢ ተሰነዘረ የተባለዉ ጥቃት በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ ሥላደረሰዉ ጉዳት በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አማኑኤል አሰፋ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት መግለጫ «ሥለደረሰዉ ጉዳት ዝርዝር መረጃ የለኝም» ብለዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት ሥለ ዛሬዉም ሆነ ሥለ ማክሰኞዉ ጥቃት በግልፅ ያለዉ ነገር የለም።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: