#Ethiopia | በአለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳውን ሲንድረም ያለባት ወጣት በህግ ትምህርት ተመርቃ የመጀመሪያዋ ጠበቃ ለመሆን በቅታለች።
ሜክሲኮ ተወልዳ ያደገችው አና ቪክቶሪያ በህይወቷ ያጋጠሟትን ሁሉ መሰናክሎች አልፋ የማይቻለውን አድርጋለች።
በአለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የዳውን ሲንድረም ያለባት ወጣት ሆና በህግ ትምህርት የተመረቀች የመጀመሪያዋ ጠበቃ በመሆን ታሪክ ሰርታለች።
አና መጀመሪያ ባመለከተችበት ዩኒቨርሲቲ በጤናዋ ምክንያት ውድቅ ተደርጋ የነበረ ቢሆንም ተስፋ ሳትቆርጥ በሌላ ተቋም ገብታ ለ5 ዓመታት በትጋት በመማር የህግ ዲግሪዋን ተቀብላለች።
አና አሁን በጠበቃነቷ ብቻ አላቆመችም የአካል ጉዳተኞችን መብት ለማስከበርና ለብዙዎች ድምፅ ለመሆን በሜክሲኮ ለፓርላማ ወንበር ለመወዳደር አቅዳለች ተብሏል።
አካላዊ ወይም አእምሮአዊ ሁኔታችን ለስኬታችን ወሰን ሊሆን እንደማይችል ቁርጠኝነትና ጠንካራ ፍላጎት ካለ የማይቻል ነገር እንደሌለ አና ማሳያ ሆናለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesge
#Downsyndrome
#Mexico #AnaVictoria
#degree #law
Source: GetuTemesgen









No comments yet.