#Ethiopia | የዚምባብዌ አሽከርካሪዎች ማህበር የአሽከርካሪነት ሙያ ህጋዊ እውቅና አግኝቶ በስርዓት እንዲደራጅና ለሙያው የመግቢያ ዝቅተኛ የትምህርት መስፈርት እንዲቀመጥ የሚጠይቅ ጥብቅ አቤቱታ ለሀገሪቱ ፓርላማ አቀረበ።
ማህበሩ ያቀረበው ይህ ጥያቄ የሙያውን ደረጃ ለማሳደግ ህጋዊ ተቆጣጣሪ ተቋም ለማቋቋም እና በዘርፉ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
የቀረበውን አቤቱታ የተቀበለው የዚምባብዌ ፓርላማ ጉዳዩን በዝርዝር መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብበት በትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ቋሚ ኮሚቴው ዘንድ መርቶታል።
ይህ የህግ ማሻሻያ ጥያቄ የመንገድ ደህንነትንና የአሽከርካሪዎችን ብቃት ያሳድጋል የሚል ተስፋ የተጣለበት ቢሆንም በሌላ በኩል ደግሞ ይፋዊ የትምህርት ማስረጃ የሌላቸው በርካታ ልምድ ያላቸው አሽከርካሪዎች ከስራ ገበያው እንዳይገለሉ የሚል ስጋት በማስነሳት በሀገሪቱ ሰፊ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.