#Ethiopia | ግሎባል ስታትስቲክስ ዋየር በአፍሪካ አህጉር ውስጥ የተሻለ እና ጥራት ያለው የከተማ መንገድ መሠረተ ልማት ያላቸው ከተሞች ደረጃ ይፋ የተደረገ ሲሆን የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕታውን እና የኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የዝርዝሩን ቀዳሚ ቦታዎች ይዘዋል።
በዚህ መሠረት የኬፕታውን ከተማ በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ፣ አዲስ አበባ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ትልቅ ስኬት አስመዝግባለች።
በዝርዝሩ መሠረት የናሚቢያዋ መዲና ዊንድሁክ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፣ የጽዳትና የከተማ ልማት አርአያ በመሆን የምትጠቀሰው የሩዋንዳዋ ኪጋሊ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ጨብጣለች።
በተጨማሪም ሌላኛዋ የደቡብ አፍሪካ ከተማ ደርባን በአምስተኛ ደረጃ ላይ ስታርፍ የሰሜን አፍሪካዋ የሞሮኮ ከተማ ካዛብላንካ ደግሞ ስድስተኛዋ ምርጥ የመንገድ መሠረተ ልማት ባለቤት ከተማ በመሆን ተመዝግባለች።
የምዕራብ እና ምስራቅ አፍሪካ ከተሞችም በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱ ሲሆን የኮትዲቯሯ አቢጃን በሰባተኛ፣ የኬንያዋ መዲና ናይሮቢ በስምንተኛ፣ እንዲሁም የጋናዋ አክራ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የአፍሪካ ምርጥ የመንገድ መሠረተ ልማት ያላቸው ከተሞች ዝርዝርን ተቀላቅለዋል።
ጂ ኤስ ደብሊው አህጉሪቱ በከተሞች መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ዝርጋታ ላይ እያሳየች ያለችውን የእድገት እንቅስቃሴ ጥሩ የሚባል ነው ብሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.