የአዲስ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት የክረምት መርሐ-ግብር አካል የሆነውን የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓልን በተለያዩ ሁነቶች ከወጣቶች ጋር በድምቀት አከበረ።
የበዓል አከባበሩ ላይ የቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የወጣት ማህበራት አባላቶች፣ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ላይ የሚገኙ ተጠቃሚዎች የከተማችን ወጣቶች በተገኙበት በአሉን በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን በክብረ በአሉ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ እንደገለጹት እንደዚህ ያሉ ድንቅ የኢትዮጵያውያን ብቻ የሆኑ በዓላቶችን ጠብቆ ማቆየት እና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም ወጣቶች እና በኪነ-ጥበብ ስራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ይህንን ከማስቀጠል አንፃር ትልቁን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ክብራለም ደምሴ በበኩላቸው የቡሄ በዓል ከክረምቱ ድቅድቅ ጨለማ ወደ ብርሃን መውጣትን የሚያሳይ፣ የአብሮነትና የአንድነት ምሳሌ መሆኑን ተናግረዋል።
የቡሄ በዓል በየዓመቱ በድምቀት የሚከበር ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊት ያለው ደማቅ በዓል መሆኑን አንስተው ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ባህሎች ባለቤት እንደመሆኗ እነዚህን ሀብቶች እንዳይበረዙ እና እንዳይረሱ መጠበቅና ማስተዋወቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዓሉ በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ፕሮግራሞች እና በባህላዊው የችቦ ማብራት ሥነ-ሥርዓት በድምቀት ተጠናቋል።



Source: FastMereja









No comments yet.