ቃላት ይነበባሉ ፣ ይሰማሉ
ቃል ስሜት ነው
ቃል ትዝታ ነው
ቃል ተስፋ ነው
ቃል ምስክርነት ነው
ቃል ማንነት ነው
ቃል ህይወት ነው
ቃል ድምፅ ነው።
“ደምፀ ቃል” የምልዕቲ ኪሮስ የግጥም መፅሀፍ፣ ቃልን ወደ ድምፅ፣ ስሜትን ወደ ግጥም፣ ግጥምን ወደ ትዝታ የሚያስጉዝ አዲስ የግጥም መድብል።
ምልዕቲ ኪሮስ በግጥም፣ በስክሪፕት ጽሑፍ፣ በዘፈን ግጥም እና በሬዲዮ ፕሮዳክሽን አቅራቢነት የተለያዩ ስራዎችን የሰራች ዘርፈ ብዙ የኪነ ጥበብ ባለሟል ።
ምልዕቲ የተለያዩ የዘፈን ግጥም ስራዎችን ለተለያዩ ታዋቂ ድምፃውያን ሰጥታለች ከነዚህም መካከል ለፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ለብስራት ሱራፌል፣ ለሄዋን ገ/ወልድ(ጃኖ) ፣ አህመድ ተሾመ ዲንቢ፣ ያሬድ ነጉ፣ ሜላት ቀለመወርቅ እና ለሌሎችም ድምፃውያን የሰጠች ሲሆን በሀገራችን የሙዚቃ ዘርፍም ላይ አሻራዋን እያኖረች ያለች ሁለገብ የኪነ ጥበብ ሰው ነች።
የግጥም ቃሏን በመጽሐፍ አትማ ከአንባቢያን ጋር ለመገናኘት ቀን ቆርጣለች።
“ደምፀ ቃል” የግጥም መፅሀፍ
ቃሉን ያንብቡ ድምፁን ያዳምጡ
ቀን- ነሀሴ 20
ሰአት- 11:30 ጀምሮ
ቦታ- በቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ አዳራሽ
#ድምፀቃል #ምልዕቲኪሮስ #የግጥምመድብል #የመጽሐፍምረቃ #ኢትዮጵያዊሥነጽሑፍ #ግጥም #ሥነጽሑፍ #EthiopianLiterature
Source: GetuTemesgen








No comments yet.