#FastMereja I በዓለም አቀፉ የመልካም ሴቶች የቁንጅና ውድድር (Miss World) ኢትዮጵያን ወክላ በመወዳደር ላይ የምትገኘው ሞዴል ሩት፣ ባገኘችው ከፍተኛ ህዝባዊ ድምፅ ከአንድ ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ8ኛ ደረጃ ወደ 2ኛ ደረጃ ማደጓ ተገለፀ።
ሞዴሏ እስከአሁን ባለው መረጃ መሠረት 98,408 ድምፆችን በማግኘት ሌሎች ሀገራት ተወዳዳሪዎችን በበላይነት በመብለጥ ደረጃዋን ማሻሻል ችላለች። ይህ አስደናቂ የስኬት ኩስረት ሊመዘገብ የቻለው በኢንተርኔት አማካኝነት በተካሄደውና የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ቀጥተኛ ተሳትፎ ባገኘው ከፍተኛ የድምፅ አሰጣጥ ዘመቻ እንደሆነ ታውቋል።
የውድድሩን የመጀመሪያ ደረጃ ለመጨበጥ በተያዘው ጥረት የኦንላይን ድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ አሁንም የቀጠለ ሲሆን፣ ደጋፊዎችና ማህበረሰቡ በተዘጋጁት ይፋዊ አገናኞች (ሊንኮች) አማካኝነት ድምፅ መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።
ሊንኩን ኮሜንት ላይ ያገኙታል 📍
Source: FastMereja









No comments yet.