በቅርቡ የመኪና መቃጠል አደጋ የገጠመው የያንጎ አሽከርካሪ ከመረቆች የ300 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍና አዲስ ስልክ ተሰጥቶታል።
ድጋፉ በአሽከርካሪው ላይ የደረሰውን ፈተና ለመቋቋም እና ለማበረታታት የተደረገ መሆኑን መረቆች ገልጸዋል።
መረቆች አሽከርካሪዎች በከባድ ጊዜ እንደሚደግፏቸው ጠቁመው፣ የአሽከርካሪዎች ደህንነት፣ ጥንካሬና ስኬት የእነርሱም ስኬት መሆኑን አስታውቀዋል።
በተለይም በአስቸጋሪ ወቅት አብሮነትና መተጋገዝ ለተጎዱ ወገኖች የሞራል እና የተግባር ድጋፍ እንደሚሆን በመግለጽ፣ “አብረን ማንኛውንም ፈተና እንሻገራለን” ብለዋል።


Source: FastMereja








No comments yet.