#Ethiopia | የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችና የአሰልጣኝ አባላት በፊፋ የረጅም ጊዜ እገዳና የገንዘብ መቀጮ ተጣለባቸው።
በቅርቡ ከተካሄደው የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ ከተፈጠሩ ውዝግቦች ጋር ተያይዞ የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች እና የቡድን አባላት ላይ ጠንከር ያሉ የዲስፕሊን እርምጃዎችን አስተላልፏል።
በዚህ ፓራዴዝ የስፔኑን ተከላካይ ኤሪክ ጋርሲያን አንገት በማነቅ እና አማካዩን ጋቪን ወደ መሬት በመወርወሩ ምክንያት የ10 ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎበታል።
ተከላካዩ ሞሊና ደግሞ የስፔኑን አማካይ ሮድሪን ሆዱን በመምታቱ የ7 ጨዋታዎች እገዳ አስተላፎበታል።
ሁለቱም ተጫዋቾች በተጨማሪነት እያንዳንዳቸው የ90,000 ዶላር የገንዘብ መቀጮ ተጥሎባቸዋል።
ሌላው ትያጎ አልማዳ የ1 ጨዋታ እገዳ እና የ30,000 ዶላር የገንዘብ መቀጮ ተጥሎበታል።
እንደዚሁም የአሰልጣኝ ቡድን አባል የሆነው ሮበርት አያላ የ3 ጨዋታዎች እገዳ እና የ30,000 ዶላር የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍል ተላልፎበታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#worldcup2026
#FIFA #BAN #Player
#Argentina #Spain
Source: GetuTemesgen









No comments yet.