#Ethiopia | የቀድሞው የኤን.ቢ.ኤ ዝነኛ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ሻኪል ኦኒል በስፖርቱ ዓለም ሊገኝ የሚችለውን ሁሉ ታላቅ ስኬት ዝና እና ከፍተኛ ሀብት ማግኘት የቻለ ሰው ነው።
አራት ጊዜ የኤን.ቢ.ኤ ሻምፒዮን ሲሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ማከማቸቱ የቅንጦት መኪኖች እና የ30 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ግዙፍ መኖሪያ ቤት ባለቤት መሆኑ የስኬቱ ማረጋገጫዎች ነበሩ።
ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ ቁሳዊ ሀብቶች በስተጀርባ ሻኪል በራሱ ስህተቶች ምክንያት የተበተነውን የቤተሰብ ህይወቱን በፀፀት ያነሳል።
በጋብቻው ወቅት ለፈጸማቸው ስህተቶች እና ታማኝ ባለመሆኑ ምክንያት ትዳሩ በመፍረሱ ሙሉ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ በግልጽ ተናግሯል።
ትዳሩ ካበቃ በኋላ ያ ግዙፍ መኖሪያ ቤቱ አዲስ መልክ ያዘ።
ሻኪል ይህንን አስመልካቶ ሲናገር፡
“በ30,000 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ቤት ውስጥ ብቻዬን ነው የምኖረው።
በወቅቱ ስህተት መስራቴ አልገባኝም ነበር ብሏል።
ይህ የሻኪል ገጠመኝ በዓለም ላይ ያሉ ማናቸውም ቁሳዊ ነገሮች ዝና እና ሀብት የቤተሰብ ፍቅር እና ሰላም ሊተኩ እንደማይችሉ ትልቅ ትምህርት የሰጠ ሆኗል።
ገንዘብ ምቾትን እንጂ እውነተኛ ደስታን እና የቅርብ ሰዎችን ፍቅር መግዛት አይችልም።
ስኬት ማለት በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ብቻ ሳይሆን ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር የምናሳልፈው ሰላም እና ፍቅር የሰፈነበት ህይወት መሆኑን የሻኪል ታሪክ ህያው ምስክር ነው።
በህይወት የምንወስዳቸው የተሳሳቱ ውሳኔዎች እስከመጨረሻው የሚከተል የፀፀት ጠጠሮችን ሊጥሉብን ይችላሉ ሲል ልምዱን አጋርቷል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#ShaquilleONeal
#success #lifestyle
#championship #cars
#fame #marriage #family
Source: GetuTemesgen









No comments yet.