የኤዝሪ ኮንሳ ወደ አርሰናል ዝውውር በይፋ ተረጋገጠ

- Advertisement -
Sidebar AD

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ኤዝሪ ኮንሳ ከአስተንቪላ አርሰናልን በረጅም ጊዜ ውል መቀላቀሉ በይፋ ተበሰረ።

የ 28 ዓመቱ ተከላካይ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ህይወቱን በቻርልተን አትሌቲክ የጀመረ ሲሆን፣ በ 2016 ዋናውን ቡድን ተቀላቅሎ አስደናቂ ብቃቱን ማሳየት ጀምሯል።

በቻርልተን ለሁለት የውድድር ዓመታት ከቆየ በኋላ በ 2018 ወደ ብሬንትፎርድ በመዛወር ያሳየው ድንቅ ብቃት በ 2019 ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ክለብ አስተንቪላ የሚያሸጋግረውን እድል ፈጥሮለታል።

በቪላ ፓርክ በቆየባቸው ባለፉት ሰባት የውድድር ዓመታት በሁሉም ውድድሮች ከ 200 በላይ ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፣ በማዕከላዊ ተከላካይነት እንዲሁም በበቀኝ መስመር ተከላካይነት የመጫወት ከፍተኛ ብቃቱ በፕሪሚየር ሊጉ ከሚገኙ ግንባር ቀደም ተከላካዮች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል።

በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የእንግሊዝን ከ 20 እና ከ 21 ዓመት በታች ቡድኖችን ወክሎ የተጫወተው ኮንሳ፣ በ 2023 ለዋናው ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ካደረገ ወዲህ በዩሮ 2024 እና በ 2026 የዓለም ዋንጫ ሀገሩን ወክሎ ተሰልፏል።

የአርሰናል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሪያ ቤርታ በዝውውሩ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት፡

“ኤዝሪ ኮንሳን ማስፈረማችን ትልቅ ደስታ ፈጥሮልናል። ኤዝሪ በአካል ብቃቱ፣ በረጋ አጨዋወቱ እና በታክቲክ ብስለቱ በፕሪሚየር ሊጉ አስተማማኝ ብቃት ከሚያሳዩ ተከላካዮች አንዱ ነው። በማዕከላዊም ሆነ በቀኝ መስመር ተከላካይነት የመጫወት ብቃቱ ለቡድናችን ትልቅ አማራጭ የሚፈጥር ሲሆን፣ ዋንጫዎችን ለማንሳት የምናደርገውን ጉዞ ያጠናክረዋል። በፕሪሚየር ሊጉና በብሔራዊ ቡድን ደረጃ በቂ ልምድ፣ የማሸነፍ ስነ-ልቦና እና የመሪነት ብቃት ያለውን ተጫዋች ወደ አርሰናል በመምጣቱ እንኳን ደስ አለህ እንላለን” ብለዋል።

ኤዝሪ ኮንሳ በአርሰናል የጀርሲ ቁጥር 15 የሚለብስ ሲሆን፣ ዝውውሩ ከሚመለከታቸው አካላት ሕጋዊ ማረጋገጫ ሲያገኝ ወዲያውኑ ከአዲሶቹ የቡድን አጋሮቹ ጋር ልምምድ የሚጀምር ይሆናል።




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2