በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 (አያት ኮንዶሚኒየም አካባቢ) ነዋሪ የሆነችው ራሄል መለሰ የተባለች ግለሰብ፣ ከሀገር ለመውጣት በሚል እቅድ ሳትታገት «ታግቻለሁ» በማለት ከቤተሰቦቿ 850 ሺህ ብር የጠየቀችው ከነአባሪዋ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ተጠርጣሪዋ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 ሰዓት ገደማ ከቤት ወጥታ ባለመመለሷ ቤተሰቦቿ ለአካባቢው ፖሊስ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ፖሊስ ማጣራት በጀመረበት ወቅትም ለአባቷ ስልክ በመደወል «ልጃችሁን ለማስለቀቅ 850 ሺህ ብር ካልላካችሁ በሕይወት አታገኟትም» የሚል የማስፈራሪያ መልዕክት ተልኮላቸዋል።
የፖሊስ የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድን ባደረገው አጣሪ ስራ፡
* የተያዙበት ቦታ፦ ባህር ዳር ከተማ «ስማዳ» ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሚገኝ ሆቴል ውስጥ፣
* የተያዙት ግለሰቦች፦ ተጠርጣሪዋ ራሄል መለሰ እና የቀድሞ የፍቅር አጋሯ ሰለሞን ቁምላቸው፣
* የወንጀሉ መንስኤ፦ ሁለቱ ግለሰቦች ከሀገር ለመውጣት ባቀዱት እቅድ መነሻነት ከቤተሰብ ገንዘብ ለማታለል የጠነሰሱት መሆኑ ተረጋገጧል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጾ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል በመሰል የሀሰት እገታ ወንጀል ውስጥ የሚገቡ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አጥብቆ አሳስቧል።
Source: Yeneta Tube








No comments yet.