ዘመን ገበያ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ» በይፋ ተከፈተ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የ2019 አዲስ ዓመት 35ኛው ዘመን ገበያ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል በይፋ ተከፈተ።

ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ታላቅ የንግድ ትርኢትና ባዛር ከ500 በላይ አምራቾችን አስመጪና ላኪዎች ይሳተፊበታል።

እንዲሁም የንግድ ወኪሎችን እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ያሳተፈ ነው ተብሏል።

በዚህ ኤክስፖ ህብረተሰቡ በቂ ጊዜ አግኝቶ በተረጋጋ ሁኔታ ግብይትና እረፍቱን እንዲያሳልፍ ሲባል የግብይት ሰዓቱ ከጠዋቱ 2:30 እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ እንዲራዘም ተደርጓል።

ተሳታፊ አጋር ድርጅቶችም ለህብረተሰቡ ተመጣጣኝ ዋጋና ልዩ ቅናሽ ለማቅረብ መስማማታቸዉ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት የንግድ እንቅስቃሴው በይፋ የተጀመረ ሲሆን ከነገ ነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ እስከ ኤክስፖው ማጠናቀቂያ ድረስ በየቀኑ የሚካሄዱ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ይጀምራሉ።

በተለይም እስከ ነሐሴ 21 ቀን ድረስ የአሸንዳ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላትን የሚያደምቁ ልዩ የባህል ጭፈራ መርሃግብሮች ለታዳሚዎች የሚቀርቡ ይሆናል ተብሏል።

ታዳሚዎች የመግቢያ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በቀላሉ መቁረጥ የሚችሉ ሲሆን በጳጉሜ 5 ቀን ምሽት በሚወጣው ዕጣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶሞቢል የBMW ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል እና ብስክሌት በሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።

የ2019 “ዘመን ገበያ” የአዲስ ዓመት ኤክስፖ በሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኢቨንትስ አዘጋጅነት የሚከናወን ይሆናል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ፎቶ፦ ከበደ መክብብ

#Ethiopia #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: