ኢትዮጵያ በኬንያ ለሚገነባው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ባለድርሻ ለመሆን ፍላጎት ማሳየቷ ተገለጸ።
አፍሪካዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ላሙ አካባቢ ለመገንባት ላቀዱትና በቀን 700,000 በርመል ነዳጅ የማጣራት አቅም ለሚኖረው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከቀረበው የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ላይ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቷ ተገልጿል።
ይህንን የገለጹት የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ አማካሪ ዴቪድ ንዲ በናይሮቢ በተካሄደ የካፒታል ማርኬት መድረክ ላይ እንደሆነ ነው ብሉምበርግ የዘገበው።
አማካሪው ከዚህ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ መቅረቡን ነው የገለጹት።
አክለውም፥ ኬንያ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን የ10 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቷንና ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳም በፕሮጀክቱ ላይ የባለቤትነት ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን በመድረኩ ተናግረዋል።
እስከ 16 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበታል ተብሎ የሚገመተው ይህ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ፣ አጠቃላይ ወጪው 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።
የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ መርሐግብሩ መስከረም ወር ላይ ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው አመላክቷል።
@Seledadotio

No comments yet.