ሊጉ ያስተዋወቃቸው አዲሶቹ ህጎች!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዘመን ዛሬ መክፈቻውን ያደርጋል።

በየሳምንቱ ከ188 በላይ በሚሆኑ ሀገራት 2.1 ቢሊዮን ተመልካቾች በቲቪ ስርጭት ጨዋታዎቹን ይመለከታሉ።

እንደ ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች ውጤቱ አስቀድሞ የሚገመት ባለመሆኑ ውድድሩ ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል።

የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክለቦች እንኳን የትኛውንም ግዙፍ ቡድን የማሸነፍ አቅም አላቸው።

ውድድሩ በስርጭት መብት ሽያጭ እና በስፖንሰርሺፕ የሚያገኘው ከፍተኛ ገቢ ዓለማችን ላይ ያሉ ምርጥ አሰልጣኞችን እና ውድ ተጫዋቾችን ሳቢ አድርጎ ለመሳብ አስችሎታል።

የጨዋታው ፈጣን እንቅስቃሴ፣ የታክቲክ ጥራት እና የደጋፊዎች ከፍተኛ ስሜት/ጫጫታ ጨዋታዎቹን እጅግ ማራኪ ያደርጋቸው ሌሎች ምክንያት ናቸው።

የክለቦቹ ታሪካዊ ባላንጣነት እና የደርቢ ጨዋታዎች የሊጉን ተወዳጅነት ያሳደጉ ጉዳዮች ናቸው።

ዛሬ በሚጀምረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አወዳዳሪው አካል የሚተግብራቸው አዳዲስ ህጎች አሉ።

ከዚህ የውድድር ዘመን ጀምሮ የክለቦች ዋና ማሊያ ላይ የውርርድ ኩባንያዎችን ማስታወቂያ መለጠፍ ተከልክሏል።

ከቡድኑ አምበል ውጭ ማንኛውም ተጫዋች ወደ ዋናው ዳኛ ቀርቦ ከተቃወመ ወይም ከከበበ ወዲያውኑ የቢጫ ካርድ ይሰጠዋል።

እንደዚሁም ግብ ጠባቂዎች ኳስ በእጃቸው ከያዙ በኋላ ከ8 ሰከንድ በላይ ካዘገዩ ለተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት የሚሰጥ ይሆናል።

የተቀየረ ተጫዋች ሜዳውን ለቆ ለመውጣት ከ10 ሰከንድ በላይ ከዘገየ የሚገባው ተጫዋች ሜዳ ከመግባቱ በፊት 1 ደቂቃ ውጭ ሆኖ እንዲጠብቅ የሚያደርግ አዲስ ህግም የሚተገበር ይሆናል።

ዛሬ በሚጀመረው የመክፈቻ ጨዋታ በለንደን ኤሚሬትስ ስታዲየም አርሰናል ከኮቬንትሪ ሲቲ ጋር ምሽት 4:00 ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#English #premierleague
#Arsenal #Manchester
#Liverpool #Chelsea


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1