#Ethiopia | የአፍሪካው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የእንግሊዙን ክለብ አርሰናልን ለመግዛት ተቃርበው የነበረ ቢሆንም ትኩረታቸውን በከፍተኛ የፋይናንስ ወጪ በሚገነባው የነዳጅ ማጣሪያ እና የማዳበሪያ ፕሮጀክታቸው ላይ ለማድረግ ሲሉ ሃሳባቸውን መቀየራቸውን ገለጹ።
በወቅቱ የአርሰናል የገበያ እሴት በ2 ቢሊዮን ዶላር ገደማ የሚገመት የነበረ ሲሆን ዳንጎቴ ክለቡን የመግዛት ፍላጎታቸውን ከዋና የንግድ ኢንቨስትመንታቸው ደህንነት ጋር በማመዛዘን ከባድ ውሳኔ ለማሳለፍ ተገደዋል።
በአህጉሪቱ ካሉ እጅግ ሀብታም ሰዎች አንዱ ቢሆኑም የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክታቸውን ለአደጋ ከማጋለጥ ይልቅ የክለቡ ታማኝ ደጋፊ ሆነው መቀጠልን እንደመረጡ ዳንጎቴ ተናግረዋል።
አሁንም ቢሆን በጨዋታ ቀናት የክለቡን ማሊያ በመልበስና ጨዋታዎችን በመከታተል አርሰናልን በከፍተኛ ፍቅር መደገፋቸውን ቀጥለዋል።
በአሁኑ ወቅት ግን የአርሰናል የገበያ ዋጋ ከበፊቱ የበለጠ በእጅጉ በመጨመሩ ምክንያት ዘንድሮ ክለቡን የመግዛት ጥያቄ መልስ አልባ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.