የዶክተር ደረጀ ዘለቀ የሁለት ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት በሀገር ፍቅር ቴአትር ተከናወነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህርና ተመራማሪ የነበሩት የዶክተር ደረጀ ዘለቀ ህልፈተ ሕይወት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት አዳራሽ ተካሂዷል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆች፣ የስራ ባልደረቦች፣ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ የዶክተር ደረጀን በጎ ስራዎች የሚያስታውሱ ንግግሮች፣ የክራር ድምፀ ውበት፣ መነባንብ እና የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ቀርበዋል።

በዕለቱ ንግግር ያደረጉ እንግዶች አባታቸው፣ ወዳጃቸውና መምህራቸው የነበረው ዶክተር ደረጀ በህግ ትምህርት ዘርፍ የነበረውን የጠለቀ እውቀትና ያበረከታቸውን የጥናትና ምርምር ስራዎች አውስተዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስሙ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን “የዶክተር ደረጀ መታሰቢያ አፀደ ህፃናትና ቤተ መጻሕፍት” ለመደገፍ የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህራን፣ ከድርጅቶችና ከግለሰቦች ጋር በመተባበር በህግ ምርምር ላይ ለተሰማሩ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግና በየዓመቱ የህግ ትምህርት ውድድር ለማዘጋጀት እቅድ መያዙን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

በዛሬው መርሃ ግብር ለህፃናት አፀደ ህፃናትና ቤተ መጻሕፍቱ ግብዓት የሚሆኑ በርካታ መጻሕፍትና የመማሪያ ቁሳቁሶች ከተሳታፊዎች መሰብሰብ ተችሏል።

ይትባረክ ዋለልኝ

#DrDerejeZeleke #MemorialProgram #AAU #LawSchool #HagerFikirTheatre #Charity #Education #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: