#Ethiopia | በብዕር ስሙ “ቃዳዊ” በመዝገብ ስሙ አረጋይ በተሰኘው ደራሲ የተጻፈው “ራሄል” አዲስ የልብ ወለድ መጽሐፍ በትናንትናው ዕለት በብላታ ህሩይ መታሰቢያ አዳራሽ በተሠጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የህትመት ብርሃን አግኝቶ ለገበያ መቅረቡ ተነግሯል።
ይህ የደራሲው የበኩር ሥራ የሆነው መጽሐፍ መቼቱ በትግራይ አድርጎ ለሴቶች እንደ ልዩ የደስታ ቀን በሚቆጠረው በአሸንዳ በዓል
መቅረቡ ተራ ግጥምጥሞሽ ሳይሆን በምክንያት ነው ተብሏል ።
ሥራው በዋናነት ራሄል በተባለች ሴት ዙሪያ የሚያጥነጠንን የፍቅር ታሪክ ይዞ የሚነሳ ሲሆን ከፍቅሩና ከውበቱ ባሻገር የሀገራችንን ሴቶች የሰላም፣ የርህራሄና የሕልም ጥሪ በስፋት ያንጸባርቃል።
መጽሐፉ የፍቅር ታሪክን ከመተርከብ በላይ በጦርነት አስከፊ ገጽታ ውስጥ ያለበደሉ ዋጋ የሚከፍለውን የወጣት ትውልድ ሀዘን በጥበብና በስነ-ጽሁፋዊ ምጥቀት ይዳስሳል።
የቀደሙት ትውልዶች በሠሩት ስህተትና ጥፋት ምክንያት የአሁኑ ወጣት ትውልድ እንዴት ላልሰራው በደል መስዋዕት እንደሚሆን የሚያሳየው ይህ ሥራ አንባቢንውን በጥበብ ፈረስ ላይ ጭኖ የሚያተም የውስጥ ስሜትን የሚነካ ታሪክ ይዟል።
መጀመሪያ ላይ በማህበራዊ ሚዲያ (በፌስቡክ) አማካኝነት በአጫጭር ጽሑፎች መልክ መቅረብ ጀምሮ የነበረው ይህ ታሪክ በብዙ አንባቢዎች ጥያቄና ድጋፍ ወደ ሙሉ መጽሐፍነት ያደገ እንደሆነ ተገልጿል።
አሁን ባለው የዲጂታል ዘመን የሰዎችን የማንበብ ልማድ ያገናዘበ አቀራረብ የተከተለው “ራሄል መቐለ” አንባቢን ሳይሰለች በፍጥነት ተነቦ እንዲያልቅ በጥንቃቄ የተቀረጸ ነው።
መጽሐፉ ለብዙ አንባቢዎች ተዳራሽ እንዲሆን ታስቦ በሶስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ ”ራሔል መቐለ” ፣ በትግርኛ ”ራሔል ጓል መቐለ” እና በእንግሊዝኛ ”Rachel: The Pearl of Northern Star” ተብለው ተዘጋጅተዋል።
የመጽሐፉ መልእክትና ታሪክ የወሰን ገደብ ሳይኖረው ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ በሦስቱም ቋንቋዎች ተተርጉሞ የቀረበ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ በጃፋር መጻሕፍት መደብር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ በኦንላይን በአማዞን አማካኝነት ለንባብ በቅቷል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen








No comments yet.