በምርጫ ተሸንፈው በሰላም የለቀቁት 25 ብቻ ሲሆኑ “አንወርድም” ያሉት ከ55 በላይ ደረሱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአፍሪካ የፖለቲካ ታሪክ በምርጫ ተሸንፈው በሰላም ስልጣናቸውን ያስረከቡ መሪዎች ቁጥር ከ25 አይበልጡም ተባለ።

በአህጉሪቱ በምርጫ ተሸንፎ ስልጣን በሰላም በማስረከብ የመጀመሪያው መሪ የሆኑት የሱማሊያው ፕሬዝዳንት
አደን አብዱላሂ ኦስማን ዳር በፈረንጆቹ 1967 ላይ ነበር።

በታሪክ በምርጫ ተሸንፈው ስልጣን በሰላም ያስረከቡ ታዋቂ የአፍሪካ መሪዎች ቁጥር ግን እስካሁን ድረስ 25 ብቻ መሆናቸው ተነግሯል።

በተቃራኒው በምርጫ ከተሸነፉ በኋላ ውጤቱን አንቀበልም በማለት ስልጣን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ያልሆኑ ወይም በኃይል ለመቆየት የሞከሩ መሪዎች ቁጥር ግን ከ35 በላይ ናቸው።

በምርጫ ከተሸነፉ ወይም የስልጣን ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አንወርድም በማለት ህገ-መንግስት በመቀየር፣ ውጤት በመሻር ወይም በኃይል ስልጣን ላይ ለመቆየት የሞከሩ መሪዎች ቁጥር ከ35 በላይ እንደሆኑ ተነግሯል።

እነዚህ አጋጣሚዎች በአህጉሪቱ የምርጫ ስርዓትና የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ላይ ትልቅ ፈተና ሆነው ያለፉ ክስተቶች መሆናቸው ነው የተገለፀው።

በሌላ በኩል የሕገ-መንግስት የስልጣን ዘመን ገደብን በመሻር አንወርድም ያሉ መሪዎች ቁጥር ደግሞ ከ20 በላይ ደርሰዋል።

የህገ-መንግስት የስልጣን ዘመንን በማሻሻልና ምርጫን በማጭበርበር አንወርድም ያሉትን ጨምሮ ግን ቁጥራቸው ከ55 በላይ ሆኗል።

የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ አሃዛዊ መረጃው በአህጉሪቱ አሁንም ቢሆን የዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታና የህግ የበላይነት አለመኖሩን ይጠቁማል ብለዋል።

በተጨማሪም ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር ባህል ገና ብዙ የሚቀረው እና ትልቅ ፈተና ያለበት መሆኑን በግልጽ ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

በአንድ በኩል ጥቂት መሪዎች የህዝብን ድምፅ አክብረው በሰላም ሲወርዱ የምናየው ተስፋ አለ።

በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኞቹ መሪዎች ስልጣንን እንደ ግል ሀብታቸው ቆጥረው ዛሬም ድረስ ሀገርና ህዝብን ለጦርነትና ለእንግልት ሲዳርጉ እያየን ነው ብለዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Africa #history #power
#conflict #constitution
#governance #policy
#Democracy #transparency


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1