ሴዶ ከግጥሚያው ሊያመልጥ አይችልም፤ ጆኒ እምቢ ቢል እንኳ ከእኔ ጋር ይደባደባል» — የETFC 2 አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ
አዲስ አበባ — በETFC 2 Cage ውድድር ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል “በተቃዋሚዬ ጆኒ ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል” በሚል ከግጥሚያው ራሱን ማግለሉን ካስታወቀ በኋላ፣ የውድድሩ አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ በሰጡት አጣዳፊ ምላሽ ሴዶ ከውድድሩ ሊያመልጥ እንደማይችልና ግጥሚያው እንደማይቀር በጽኑ አስታወቁ።
የውድድሩ አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ፣ ሴዶ አሁን ላይ ጨርቅ እየወረወረና የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደረ ከውድድሩ ለመውጣት ቢሞክርም በህግና በውል የተያዘ በመሆኑ ከፋይቱ ማምለጥ እንደማይችል ገልጸዋል። “ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በሚከታተለው ውድድር ላይ እንደዚህ አይነት ሰበብ አያመልጥም” ያሉት አዘጋጁ፣ ሴዶ ከሀገር እንዳይወጣ በኤርፖርትና አስፈላጊ ቦታዎች ላይ የደህንነት ጥበቃ ክትትል እንዲደረግ መደረጉንም አብራርተዋል።
በተጨማሪም አዘጋጁ ሁኔታውን በቁጣና በቀልድ አቀላቅለው ሲናገሩ «ሴዶን ጆኒ እንኳ እምቢ ብሎ የማይደባደበው ከሆነ፣ ከእኔ ጋር ይደባደባል፤ ከእኔ ጋር ይገጥማል!» በማለት ውድድሩ በማንኛውም ሁኔታ እንደማይቀርና Cage ውስጥ መግባቱ ግዴታ እንደሆነ አጥብቀው ገልጸዋል።
የETFC 2 Cage ውድድር የታቀደበት ቀንና ሰዓት ሳይቀየር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አረጋግጠዋል።
Via: ETFC 2
@Seledadotio

No comments yet.