ከ9 ሚሊዮን በላይ መኖሪያ ቤቶች ወራሽ አጥተው ባዶአቸውን ቀሩ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በጃፓን ገጠራማ አካባቢዎች የሚገኙ ከ9 ሚሊዮን በላይ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወራሽ አጥተው ባዶአቸውን ቀርተዋል።

በሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር እድሜ እየገፋ መምጣቱን ተከተሎ አረጋውያን ሲያልፉ ቤቶቻቸው ለልጆቻቸው ቢወረሱም ተረካቢ ግን አልተገኘም።

አብዛኞቹ ወጣቶች በቶኪዮ እና ኦሳካ ዋና ዋና ከተሞች ላይ ኑሯቸውን በማድረጋቸው ወደ ገጠር ተመልሰው መኖር አልቻሉም።

ወጣቶች ለትምህርትና ለሥራ እድል ወደ ትልልቅ ከተሞች እንደ ቶኪዮ በመሄዳቸው ገጠራማና ትንንሽ ከተሞች ባዶ እየሆኑ ይገኛል።

በጃፓንኛ “አኪያ” በመባል የሚታወቁት እነዚህ ቤቶች ባለቤቶቻቸው ከባድ የታክስ እና የጥገና ወጪን ለማስቀረት በቅናሽ ዋጋ እየሸጡ ይገኛሉ።

ሌላው ምክንያት በጃፓን የውልደት መጠን በመቀነሱና የዕድሜ ባለጸጎች ቁጥር በመጨመሩ የመጣ ነው ተብሏል።

በዚህም ምክንያት በርካታ የጃፓን ገጠራማ መንደሮች ቀስ በቀስ ነዋሪዎቻቸውን በማጣት ላይ ናቸው ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Japan #House #Birthrate
#Osaka #Tokyo #Deathrate


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: