የ አርዳይታ ተወላጆች ከ10፣ 20፣ እና 30 ዓመታት በኃላ ሊገናኙ ነዉ ::
የሀገሪቱ ተወላጆች ለአከባቢያቸዉ ”አርዳይታና አከባቢዋ በጎ አድራጎት ማህበር” የተሰኘ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት “NGO” አቋቋሙ ::
በሀገሩ ተወላጆች የተቋቋመዉ ይህ ድርጅት የአከባቢው ማህበረሰብን በትምህርት ፣ በጤና፣ በአከባቢ ጥበቃ፣ በኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ስራዎችን ለመስራት እንዲሁም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ አረጋዉያን እና ህፃናት ለመንከባከብ ያለመ ነዉ!
ማህበሩ ከ9 መቶ በላይ የሚደርሱ አባላት ያለዉ ሲሆን እኚህም በአርዳይታ የተወለዱ፣ ያደጉ፣ የተማሩ፣ የሰሩ እና የኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ናቸዉ ::
ቅዳሜ ነሀሴ 23 እና እሁድ ነሀሴ 24 ትልቅ ድግስ አዘጋጅቷል ።
በዚህም የ ድርጅቱ የመክፈቻ መርኃግብር ይደረጋል። በመርሀግብሩ ላይ የወረዳ አመራሮች የኮሌጁ ዲን፣ የምርጥ ዘር እርሻ ልማት ሀላፊ ፣ አባገዳ ሀደሲንቄ እንዲሁም ከሀገር ዉስጥ እና በዉጪ ሀገራት የሚኖሩ የአርዳይታ ተወላጆች ይገኛሉ!
በእለቱ የአረንጓዴ አሻራ መርኃግብር ፣ የሩጫ ፣ እንዲሁም የመምህራን ፣ የተማሪዎች እዉቅና እና የተለያዩ መርኃግብር ይኖራሉ !
ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አከባቢዉን ለመርዳት የተቋቋመ ቢሆንም ሌሎች የማህበረሰብ ክፍልንም ተጠቃሚ ያደርጋል::
በቅርቡም ህጋዊ ለመሆን ችሏል ፍቃድ እስኪያገኝም ድረስ የታመመን መርዳት የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ማገዝ የመሳሰሉ ስራዎች ተሰርተዋል !
አከባቢዉ ምዕራብ አርሲ ዉስጥ የሚገኝ ሲሆን በ1970ዎች መጀመሪያ የተቋቋመዉና አሁን በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ስር በሚተዳደረዉ አርዳይታ ግብርናና ቴክኒክ ሞያ ኮሌጅ እንዲሁ በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ስር በሚተዳደረዉ የአርዳይታ ምርጥ ዘር ድርጅት ይታወቃል ::
Via Fetia Hussen



Source: FastMereja







No comments yet.