#Ethiopia | የድምጻዊት ተዓምር ግዛው “በፍቅር” የተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ለጆሮ ሊበቃ መሆኑ ሰምተናል።
ድምጻዊት ተአምር ግዛው ለአራት ዓመታት ስትሰራው የቆየችው “በፍቅር” የተሰኘ የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሟን ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ለአድማጮች በይፋ እንደምታበቃ አስታወቀች።
አልበሙ በድምጻዊቷ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል እና በተለያዩ የሙዚቃ ማደመጫ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል ተብሏል።
ይህ የድምጻዊቷ የመጀመሪያ አልበም አጠቃላይ 16 የሙዚቃ ሥራዎችን የያዘ ሲሆን፣ በውስጡም የጓይላ (ትግርኛ)፣ የፎሌ (ኦሮምኛ) እና ሌሎች ህብረ ብሄራዊ ስልተ-ምቶች ይዟል።
እንዲሁም በኦሮምኛ እና በትግርኛ ቋንቋዎች የተሰሩ ሙዚቃዎች ተካትተውበታል።
በተጨማሪም ከአልበሙ ውስጥ ለአንዱ ሙዚቃ የተሰራ የቪዲዮ ክሊፕ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ መገባደዱ ተገልጿል።
በአልበሙ ዝግጅት ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች በርካታ ሲሆኑ፣ የዜማ ደራሲያን አበበ ብርሃኔ፣ እሱባለው ይታየው፣ ምሕረታብ ደስታ፣ አቤል ሙሉጌታ፣ ቢንያምር አሕመድ እና ዳን አድማሱ ናቸው።
የግጥም ደራሲያን ደግሞ ወንድወሰን ይሁብ፣ ዳን አድማሱ እና ጎይትኦም ሃይለማርያም ናቸው።
በሙዚቃ ቅንብር ሚካኤል ሃይሉ (ሚኪ ጃኖ)፣ ታምሩ አማረ፣ ብሩክ አፈወርቅ እና ሌሎችም ተሳትፈዋል።
የ16ቱ ሙዚቃዎች ማስተሪንግ (Mastering) በኪሩቤል ተስፋዬ ተሰርቷል።
ስራውን አስመልክቶ የሙዚቃ አቀናባሪው ሚካኤል ሃይሉ (ሚኪ ጃኖ) “ያንጻሉ፣ ያዝናናሉ፣ ያክማሉ ብለን የሰራናቸውን ሙዚቃዎች ለአድማጮች እናበረክታለን ብለዋል።
አስተማሪም አስደሳችም የስራ ጊዜ አሳልፈን ለዚህ በመብቃታችን አድማጮች ልባዊ አስተያየታቸውን ለድምጻዊዋ እንዲለግሱ እጠይቃለሁ” ብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen



Source: GetuTemesgen









No comments yet.