#Ethiopia | በአንድ ወቅት ጫማ እንኳ ማድረግ የማይችል ድሃ ልጅ የነበረው ሲም ዎንግ ሁ በኋላ ላይ የዓለምን የኮምፒውተር ኦዲዮ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ በመቀየር የቢሊየን ዶላር ባለቤት መሆን ችሏል።
“የሲንጋፖር የቴክኖሎጂ አባት” በመባል የሚታወቀው የዚህ ታላቅ ሰው የህይወት ጉዞ ለብዙዎች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።
ሲም ዎንግ ሁ የተወለደውና ያደገው በሲንጋፖር ገጠራማ መንደር ውስጥ ሲሆን ቤተሰቦቹ በዶሮና አሳማ እርባታ የሚተዳደሩ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነበሩ።
የዕለት ተዕለት ህይወቱ በከባድ ድህነት የተከበበ ቢሆንም ላቅ ያለ የትምህርት ፍላጎት እና የቴክኖሎጂ ስሜት ነበረው።
በኤሌክትሪካል ኤንጂነሪንግ ዲፕሎማውን ካጠናቀቀ በኋላ የወደፊት እጣ ፈንታውን በራሱ እጅ ለመጻፍ ወሰነ።
በ1981 እ.ኤ.አ. ሲም ዎንግ ሁ ከሁለት የልጅነት ጓደኞቹ ጋር በመሆን በ6,000 ዶላር መነሻ ካፒታል creative technology የተባለችውን ኩባንያ አቋቋመ።
በወቅቱ ኮምፒውተሮች ድምፅ የማውጣት አቅማቸው እጅግ ዝቅተኛ ነበር።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ በፈረንጆቹ በ1989 sound blaster የተባለውን የኮምፒውተር ድምፅ ካርድ ለዓለም አስተዋወቀ።
ይህም ፈጠራ ኮምፒውተሮች ጥራት ያለው ድምፅ ሙዚቃ እና የጨዋታ ኦዲዮዎችን እንዲያወጡ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ አብዮት ፈጠረ።
በዚህ ስኬቱም ኩባንያው በአሜሪካው ናስዳቅ (NASDAQ) የአክሲዮን ገበያ ላይ የተመዘገበ የመጀመሪያው የሲንጋፖር ኩባንያ ለመሆን በቅቷል።
ሲም ዎንግ ሁ በቴክኖሎጂው ዓለም የማይበገር ተወዳዳሪ ነበር።
ኩባንያው ከአፕል iPod በፊት ዲጂታል የሙዚቃ ማጫወቻዎችን ለገበያ ያቀረበ ሲሆን አፕል በፈጠራ መብቱ ላይ ባደረገው ጥሰት ምክንያት ክስ መስርቶ 100 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ ማሸነፍ ችሏል።
የሲንጋፖርን የቴክኖሎጂ መሪ በመሆን መንገድ የጠረገው ሲም ዎንግ ሁ በ2023 በተወለደ በ67 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Singapore #fathertechnology
#creativetechnology
#Soundblaster #NASDAQ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.